"ደጆችሽ አይዘጉ"መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር

ስለ ማህበሩ

"ደጆችሽ አይዘጉ"መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር በጅማ ሀገረ ስብከት በህጋዊ መንገድ በ1998 ዓ.ም. ተቋቋመ። ማህበሩ የተዘጉ 142 አብያተ ክርስቲያናትን አስከፍቷል ፣በጅማ ገጠር ውስጥ በ22 ወረዳዎች ላይ በአካባቢው ቋንቋ የሚሰብኩ 44 ደቀመዛሙርት በማሰልጠን እና በማሰማራት ስብከተ ወንጌልን እንዲስፋፋ አድርጓል። እንዲሁም በጅማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገለግል የሰባክያን ማሰልጠኛ ተቋም በ4 ሚሊዮን ብር በመገንባት አስመርቆ ለስራ አብቅቷል፣ የገጠሯ ቤተ ክርስቲያን በልማት እራሷን በማስቻል ከልመና የምትላቀቅበትን የልማት ፕሮጀክት በመንደፍ በፍራፍሬ ልማት፣ በንብ ማነብ፣ በቡና ልማት እና በወፍጮ ስራ ከ30 ደብራት በላይ ከሚገኘው ገቢ እንዲጠቀሙ እየተደረገ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የማህበሩ ትልቁ ልማት በጅማ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሁለገብ ህንጻ ሲሆን ይህንን ህንፃ ከፍፃሜ ለማድረስ በጥቅሉ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል።

ራዕይ

በተለያዩ ምክንያቶች የተዘጉ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተከፍተው ራሳቸውን በሚያስችል ዘላቂ ልማት ከተረጂነት ተላቀው በሙሉ አቅማቸው መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡ ማየት ነው።

አላማ

1. በገጠር የተዘጉ አብያተ ክርሰቲያናትን ማስከፈት
2 ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት
3 በልማት ራስን ማስቻል
*** ለድንገተኛ አደጋ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ድጋፍ ማድረግ

የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶች

የአንድ ብር ለአንድ ገጠር ቤተ ክርስቲያን በወር በመለገስ መደገፍ 

 

በቋሚ ትዕዛዝ ከተቀማጭ የባንክ ሂሳብ ቆራጭ በማድርግ የመደገፍ ዘዴ፡፡

 

ሰዎች በሞያቸው አገልግሎት የሚሰጡበት ስልት
የባላ 500 እና 1000 ብር የበረከት ሰርተፍኬት ሽያጭ
  • በጅማ ከተማ ውሃ ልማት አካባቢ የሚገኘውን 2270 ሜ.ካ ቦታ በ750ሺ ብር በሚያዚያ 2003 ዓ.ም. ግዥ ተፈፀም።
  • ግንባታው ጥቅምት 26 2009 ዓ.ም. በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀ/ስበከት ሊቀጳጳስ በፀሎት ተባርኮ ተጀመረ።
  • በጥቅሉ ቀሪው ስራ በመሀንዲሶች ግምት ከ 40  ሚሊዮን ብር በላይ  ይፈልጋል።
  • የገበያ ማዕከል ግንባታው ሲጠናቀቅ በጅማ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የተቸገሩ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ድጎማ በማድረግ የሚኖረው አስተዋፆ እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህም በትንሹ ከ100 በላይ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እና የስብከተ ወንጌል ተቋሙ ይደገፉበታል።
  • በርካታ ፋይዳ ያለው ይህ ህንጻ ቶሎ ለማጠናቀቅ የግንባታ ፌሮ ብረት ሲሚንቶ  ጠጠር አሸዋ የባለሞያ ጉልበት እና ሌሎች ክፍያዎች ይጠበቃሉ። ለዚህ ታሪካዊ ስራ የበኩልዎን ድርሻ ዛሬ ነገ ሳይሉ ይወጡ።

በጅማ ሀገረ ስብከት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ዛሬ ላይ ያሉበት ሁኔታ

በ2001 ዓ.ም. በጅማ ሀገረ ስብከት ከነበሩት 283 አብያተ ክርስቲያናት 142 የተዘጉ ነበሩ። በአሁኑ ሰዓት 403  አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን ከ2001 ዓ.ም ወዲህ ብቻ 120  አዳዲስ አብያተ ክርሰቲያናት ተሰርተዋል። በአሁኑ ሰዓት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ብዙ ጥረት ተደርጓል።

0
በጅማ ገጠር ውስጥ በ 22 ወረዳዎች ላይ በመዘዋወር የተዘጉትን አስከፍቷዋል እያሰከፈተም ይገኛል፡፡
0 +
በአካባቢው ቋንቋ የሚሰብኩ 44 ደቀ መዛሙርት አፍርቷል፡፡
0 +
ከ 70 በላይ የዳቆናት ደሞዝ በመክፈል እንዲያገለግሉ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
0 +
የካህናት ደሞዝ በመክፈል እንዲያገለግሉ ሲያደርግ ቆይቷል
አድራሻ
አዲስ አበባ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ህንፃ 4ኝ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42/3B
ስልክ
  • 0118 95 93 73
  • 0926692020
  • 0911201649
  • 0911688464
    ጅማ ውሃ እና ፍሳሽ አከባቢ
    ስልክ
  • 0472111515
  • 0967104647
  • Scroll to Top